በድሬዳዋ እየተገነቡ ያሉ አገልግሎት መሥጫ ተቋማት የሕብረተሰቡን ተሳትፎ እንደሚያሳድጉ ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር እና በሕዝቡ ትብብር እየተገነቡ ያሉ ተቋማት የሕብረተሰቡን ተሳትፎ በእጅጉ ሊያሳድጉ የሚችሉ መሆናቸው ተገለጸ፡፡
የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች ቡድን በሁለተኛ ቀን የጉብኝት ቆይታው በድሬዳዋ ከተማ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎችን ጎብኝቷል፡፡
በዚህም በዛሬው ዕለት ቡድኑ የድሬዳዋ የወጣቶች ስፖርት አካዳሚን፣ የድሬዳዋ ስታዲየም ማሻሻያ ፕሮጀክትን፣ የድሬዳዋ ደወሌ ምድር ባቡር ድርጅትን እና የሳቢያን አጠቃላይ ሆስፒታልን የኩላሊት እጥበት ማዕከል ጎብኝቷል፡፡
የጉብኝቱ መርሐ-ግብር የተሰናዳው የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር መሆኑ ተገልጿል፡፡