Fana: At a Speed of Life!

የምርት አቅርቦትን በሚደብቁ የሕብረት ስራ ማህበራትና ነጋዴዎች ላይ ቁጥጥር እንደሚደረግ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የምርት አቅርቦትን በሚደብቁ የሕብረት ስራ ማህበራት እና ነጋዴዎች ላይ ቁጥጥር እንደሚደረግ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር አባይ ገለጹ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማዋ የሚስተዋለውን የኑሮ ውድነት ለማረጋጋት ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመቀናጀት የኑሮ ውድነት እና ገበያ ማረጋጋት ግብረ ሃይል በማቋቋም እየሰራ እንደሚገኝ ተመላክቷል፡፡

በቀጣይ የሚከበሩ በዓላትን ምክንያት በማድረግ የሚፈጠርን የምርት አቅርቦት ችግር ለመፍታት ዛሬ ምክትል ከንቲባ እና የስራ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ጃንጥራር አባይ በተገኙበት  ከኑሮ ውድነት እና ገበያ ማረጋጋት ግብር ኃይል ጋር ውይይት ተካሂዷል፡፡

በዚህም ግብረ ኃይሉ በመጪው የፋሲካና  የኢድ አል ፈጥር በዓላት ላይ ሕገ-ወጥ የዋጋ ጭማሪና ደረሰኝ ግብይት፣ በሕገ-ወጥ መንገድ የሚካሄድ የምርት ዝውውር እንዲሁም የምርት ክምችትን ለመከላከል የመጋዘን ፍተሻ የግብረ ኃይሉ ዋና ተግባር እንደሚሆንም ተጠቁሟል፡፡

የኢንዱስትሪ ምርቶች እንደ ፓስታ እና ማካሮኒ ምርቶች በስፋት እየቀረቡ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን÷የምርት አቅርቦት  ችግር እንደማይኖር መጠቀሱንም የቢሮው መረጃ ያመላክታል፡፡

ግብረ ሃይሉ ከተቋቋመ ጀምሮ የምርት አቅርቦት፣ ጥራትና ዋጋ መሻሻል እንደታየ የገለጹት አቶ ጃንጥራር÷የስራ ሃላፊዎች፣ የንግድ ኃላፊዎችና ማህበራት ከምርት አቅርቦት ከጥራትና ዋጋ አንጻር ብዙ መስራት እንደሚገባቸው አሳስበዋል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.