Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ጸጋአብ ከዓለም አቀፉ የአዕምሯዊ ንብረት ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጄኔቫ የኢፌዴሪ ቋሚ ተጠሪ አምባሳደር ጸጋአብ ከበበው ከዓለም አቀፉ የአዕምሯዊ ንብረት ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዳረን ታንግ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም ኢትዮጵያና የዓለም አቀፉ የአዕምሯዊ ንብረት ድርጅት በቀጣይ በትብብር በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

አምባሳደር ጸጋአብ÷ዓለም አቀፉ የአዕምሯዊ ንብረት ድርጅት ለኢትዮጵያ እያደረገ ላለው እገዛ አመስግነው ድጋፉ ይበልጥ ተጠናክሮ እዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡

ድርጅቱ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ በተለይም የግብርና ምርቶችን በዘመናዊ አሰራር በማዘመንና ዓለም አቀፍ እውቅና እንዲያገኙ ለማድረግ በዘርፉ ለተሰማሩ ባለሃብቶች ስልጠና እየሠጠ እንደሚገኝ ተጠቅሷል፡፡

በተጨማሪም ለሀገር በቀል እውቀት እና የቴክኖሎጂ ፈጠራ ባለቤቶች፣ ለባህል መድኃኒት አዋቂዎችና በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ለሚሰሩ ባለሙያዎች የአጭር እና የረጅም ጊዜ ስልጠና ይሰጣል ተብሏል፡፡

የተለያዩ የቴክኖሎጂ እና የፈጠራ ተቋማት እንዲጠናከሩ የገንዘብ፣ የቁሳቁስ እና የቴክኒክ እገዛዎችን እያደረገ መሆኑንም በጄኔቫ ከኢፌዴሪ ቋሚ ተጠሪ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.