የ2024ቱ የአፍሪካ ዋንጫ የሚካሄድበት ቀን ይፋ ሆነ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)በኮትዲቯር አስተናጋጅነት የሚካሄደው የ2024ቱ የአፍሪካ ዋንጫ የሚካሄድበት ወር እና ቀናቶች በአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ይፋ ተደርገዋል፡፡
ካፍ በትናንትናው እለት እንዳስታወቀው÷ የ2024ቱ የአፍሪካ ሀገራት እግር ኳስ ውድድር ከፈረንጆቹ ጥር 13 እስከ የካቲት 11 ቀን 2024 ይካሄዳል፡፡
እስካሁን ባለው የሀገራቱ የማጣሪያ ውድድር አልጀሪያ፣ ሞሮኮ፣ ደቡብ አፍሪካ እና ሴኔጋል ከአስተናጋጇ ኮትዲቯር ጋት ለውድድሩ ቀድመው ማለፋቸውን ያረጋገጡ ቡድኖች ናቸው።