Fana: At a Speed of Life!

የተመዘገቡ ውጤቶችን ለማስቀጠል መንግስት በቁርጠኝነት እንደሚሠራ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በለውጡ ሂደት በሁሉም መስክ የተመዘገቡ ውጤቶችን ለማስቀጠል መንግስት በላቀ ብቃትና ቁርጠኝነት እንደሚሰራ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ ቤልጂጌ ገለጹ፡፡

አቶ ተስፋዬ በለውጡ ሂደት ባለፉት አምስት ዓመታት በፖለቲካው መስክ የተከናወኑ ስራዎችን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በማብራሪያቸውም በኢትዮጵያ ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ የዘለቁትን የእኩልነት፣ የፍትሐዊ ተጠቃሚነትና የዴሞክራሲ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተሰሩትን ዋና ዋና ተግባራት አንስተዋል፡፡

የብሄር፣ የሃይማኖት፣ የቋንቋ፣ የባህልና ማንነት ጥያቄዎች ምላሽ ሳይሰጣቸው ለዘመናት መዝለቃቸውን አስታውሰው ባለፉት አምስት ዓመታት ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራትን ዘርዝረዋል።

በተለይም የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችና የዴሞክራሲ መብቶች ጭላንጭል መጥፋት ሌላኛው ችግር እንደነበር ጠቅሰው በለውጡ በተከናወኑ ስራዎች ተጨባጭ ውጤቶች የተመዘገቡበት ስለመሆኑ አስረድተዋል።

ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ በኢትዮጵያ ፍትሐዊ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት እውን እንዲሆን መንግስት በስፋት መስራቱን ገልጸዋል።

ሀገራዊ ለውጡ ኢትዮጵያን ገጥመዋት ከነበሩት ውስብስብ የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ችግሮች ያሻገራት መሆኑን ጠቁመው÷ በሁሉም መስኮች የተገኙ ውጤቶች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በለውጡ ሂደት በሁሉም መስክ የተመዘገቡ ውጤቶችን ለማስቀጠል መንግስት በላቀ ብቃትና ቁርጠኝነት የሚሰራ መሆኑንም አረጋግጠዋል።

ሀገራዊ ምርጫ ከተደረገ በኋላ የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች በመንግስት ስልጣን ቦታ ያገኙበት አዲስ የፖለቲካ ምዕራፍ መከፈቱን ገልጸዋል።

በለውጡ በተለይም በፖለቲካው መስክ የነበረውን ምስቅልቅል ችግርና አግላይነት በማስቀረት ሁሉንም ያሳተፈ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ መሰረት ማኖር ተችሏል ነው ያሉት፡፡

በኢትዮጵያ የምርጫ ታሪክ በተለየ መልኩ ዴሞክራሲያዊ፣ ነፃና ሰላማዊ ምርጫ መከናወኑን አስታውሰዋል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.