Fana: At a Speed of Life!

በአማራ እና ደቡብ ክልሎች በደረሱ የትራፊክ አደጋዎች የስምንት ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ እና ደቡብ ክልሎች በደረሱ ሁለት የትራፊክ አደጋዎች የስምንት ሰዎች ህይወት አለፈ።

በአማራ ክልል አዊ ዞን ባንጃ ወረዳ ዚቅ ጎመርታ ቀበሌ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአምስት ህጻናትና መምህርት ህይወት አልፏል።

አደጋው በዛሬው እለት በባንጃ ወረዳ ዚቅ ጎመርታ ቀበሌ 2:00 ሰአት አካባቢ የዳሳሽ አካዳሚ ትምህርት ቤት ተማሪዎችን ወደ ቻግኒ ታሪካዊ ቦታዎች ለማስጎብኘት ይዞ እየሔደ የነበረ ተሽከርካሪ በመገልበጡ የደረሰ መሆኑን የባንጃ ወረዳ ኮሙኒኬሽን አስታውቋል።

በደረሰው የትራፊክ አደጋ የሶስት ህፃናት ህይወት ወዲያው ሲያልፍ አንድ ህፃንና እና አንዲት መምህር ህክምና እንደደረሱ ህይወታቸው አልፏል።

ሌሎች ከባድና ቀላል ጉዳት የደረሰባቸው ህፃናት ወደ እንጅባራ ጠቅላላ ሆስፒታል ገብተው ህክምና እየተደረገላቸው ይገኛል ።

በተመሳሳይ በጌዴኦ ዞን በወናጎ ከተማ በተከሰተ የትራፊክ አደጋ የሶስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በ10 ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡

አደጋው የደረሰው ትናንት ምሽት 12 ሰዓት አካባቢ መነሻውን ያቤሎ አድርጎ ወደ አዲስ አበበ ሲጓዝ የነበረው መኪና በተቃራኒ አቅጣጫ ሲጓዝ ከነበረው አነስተኛ የህዝብ ማመላለሻ ተሸከርካሪ ጋር በመጋጨቱ ነው፡፡

በዚህም የሶስት ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ በስድስት ሰዎች ላይ ከባድና በአራት ሰዎች ላይ ቀላል ጉዳት መድረሱ ተገልጿል፡፡

በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎችም በዲላ ሪፈራል አጠቃላይ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ከጌዴኦ ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.