Fana: At a Speed of Life!

የሲቪል ማሕበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን፣ የክልልና የፌደራል ባለድርሻ አካላት ጉባኤ እተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 7ኛው የሲቪል ማሕበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን፣ የክልልና የፌደራል ባለድርሻ አካላት ጉባኤ በሚዛን አማን ከተማ እተካሄደ ነው፡፡

በመድረኩ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር) ፣ የመንግስት ዋና ተጠሪ ፀጋዬ ማሞ፣ የፍትሕ ሚኒስትር ዴኤታ ዓለምአንተ አግደው፣ የክልሎች የፍትሕና የፋይናንስ ቢሮ ኃላፊዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር)÷ የሕዝብና የመንግስት በጀት በማይደርስባቸው ስራዎች ላይ የሲቪል ማሕበረሰብ ድርጅቶች የሚያደርጉት አስተዋጽኦ የጎላ መሆኑን ተናግረዋል ።

ተቋማቱ በክልሎች ያሏቸው ስብጥር የተመጣጠነ እንዲሆን የፌደራል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ሊሰራበት ይገባል ማለታቸውን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

ዓለምአንተ አግደው እንዳሉት÷ የሲቪል ማሕበረሰብ ድርጅቶች የተቋቋሙለት ዓላማን እንዲዲያሳኩ በመደገፍ፣ በመከታተልና በመቆጣጠር ኃላፊነት ያሉባችሁ አካላት ቅንጅታዊ አሰራርን በማጎልበት መንቀሳቀስ ያስፈልጋል፡፡

የኢፌዴሪ ሲቪል ማሕበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ጂማ ድልቦ÷ የሲቪል ማሕበረሰብ ድርጅቶች ለተጀመረው የለውጥና የዲሞክራሲ ስርዓት ግምባታ የበኩላቸውን ድጋፍ እንዲያበክቱ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.