የሀገር ውስጥ ዜና

በማደያዎች የነዳጅ ግብይትን በዲጂታል የማካሄድ ሥራ ተጀመረ

By Tamrat Bishaw

March 31, 2023

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በማደያዎች የነዳጅ ግብይትን በዲጂታል የማካሄድ የሙከራ ትግበራ ሥራ ተጀምሯል፡፡

ከግንቦት 1 ቀን 2015 ዓ.ም ደግሞ በመላ ሀገሪቱ የዲጂታል የነዳጅ ግብይት ይጀመራል ሲሉ የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ(ዶ/ር) ተናግረዋል።

ዛሬ በመዲናዋ ለሙከራ የተጀመረው የዲጂታል ግብይት በሁሉም ተሽከርካሪዎች እና በሁሉም ማደያዎች ተግባራዊ ይሆናል ብለዋል ሚኒስትሩ።

ግብይቱ በዲጂታል መሆኑ ምርት እንዳይባክን እና የተሳለጠ ግብይት እንዲኖር ያደርጋልም ብለዋል።

የነዳጅ ግብይቱ በቴሌብር አማራጭ የሚከናወን መሆኑን ያነሱት ሚኒስትሩ በዚህ የዲጂታል ክፍያ ስርዓት ሁሉም የመንግስት እና የግል ተሽከርካሪዎች ቁጥጥር ይደረግባቸዋል ብለዋል።

በቅርቡም የትራንስፖርት ትኬት በዲጂታል እንደሚጀመር ተናግረዋል።

በመሳፍንት እያዩ