Fana: At a Speed of Life!

በኮንሶ ዞን በድርቅ ምክንያት ለችግር ለተጋለጡ ወገኖች ድጋፍ እየቀረበ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል ኮንሶ ዞን በተከሰተው ድርቅ ለችግር ለተጋለጡ ወገኖች ድጋፍ እየቀረበ መሆኑን የዞኑ አስተዳደር አስታወቀ፡፡

የዞኑ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ ሠራዊት ዲባባ እንዳሉት÷ የተከሰተውን የድርቅ ጉዳት ተከትሎ የፌደራል መንግስት፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ የደቡብ ክልል እና ሌሎች ተቋማትና የሕብረተሰብ ክፍሎች እስካሁን ከ15 ሺህ በላይ ኩንታል ድጋፍ አድርገዋል፡፡

ድጋፉም ስንዴ፣ በቆሎ እንዲሁም የስንዴ እና የበቆሎ ዱቄት መሆኑን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

በዚህም እንደዞን ለችግሩ ከተጋለጡ ከ227 ሺህ በላይ ወገኖች ከ90 ሺህ በላይ ለሚበልጡት ወገኖች ድጋፉ ተደራሽ ተደርጓል ብለዋል፡፡

እንዲሁም የኦሮሚያ ክልል ቡሳ ጎኖፋ ቃል ከገባው 5 ሺህ ኩንታል ድጋፍ ዛሬ 2 ሺህ ኩንታል የበቆሎ ዱቄትና እና ጥሬ ቦቆሎ ማስረከቡን ገልጸዋል፡፡

ቀሪውም በሁለት ቀናት ውስጥ እንደሚገባ ይጠበቃል ነው ያሉት፡፡

ከድጋፍ አድራጊዎች ወደ ዞኑ በመጓጓዝ ላይ ያሉ ድጋፎች መኖራቸውንም ነው የጠቆሙት፡፡

እስካሁን ድጋፍ ላደረጉ አካላት ምስጋና ያቀረበው ዞኑ÷ አሁንም ለችግር ከተጋለጠው የዞኑ ነዋሪዎች ብዛት አንጻር የቀረበው በቂ ባለመሆኑ እና ሁሉንም ተደራሽ ባለማድረጉ ድጋፉ እንዲጠናከር ጥሪ አቅርቧል፡፡

እንዲሁም ዞኑ ከ4 ነጥብ 1 ሚሊየን በላይ የእንስሳት ሃብት እንዳለው ጠቁመው በድርቁ ምክንያት ከ3 ሺህ 600 በላይ እንስሳት መሞታቸውን ጠቅሰዋል፡፡

የከፋ ጉዳት እንዳይከሰትም ለእንስሳት የሚሆን የመኖ ድጋፍ እንዲደረግ ጠይቀዋል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.