Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል የ279 የመስኖ ፕሮጀክቶች ግንባታ እየተከናወነ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ከ1 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በሚበልጥ ወጪ 279 አነስተኛና መካከለኛ የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶች ግንባታ እየተከናወነ መሆኑን የክልሉ መስኖና ቆላማ አካባቢ ልማት ቢሮ ገለጸ፡፡

የቢሮው ምክትል ኃላፊ አየልኝ መሳፍንት እንዳሉት ዘመናዊ የመስኖ ልማት አውታሮችን በማስፋፋት የክልሉን አርሶ አደር የልማት ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ ነው።

የመስኖ አውታር ዝርጋታ ግንባታዎቹ አርሶ አደሩን ከዝናብ ጥገኝነት በማላቀቅ በመስኖም ማምረት እንዲችል ያግዛሉ ብለዋል፡፡

በተያዘው በጀት ዓመት 1 ቢሊየን 470 ሚሊየን ብር በጀት ተመድቦ በተለያየ ምክንያት ያልተጠናቀቁ ነባርና አዳዲስ የመስኖ ፕሮጀክቶች ግንባታ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።

እየተገነቡ ካሉት 89 ፕሮጀክቶች መካከል ዘንድሮ አዲስ የተጀመሩ አነስተኛና መካከለኛ ፕሮጀክቶች መሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ቀሪዎቹ ቀደም ሲል ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶች እንደሆኑ ኃላፊው ገልጸዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.