በሕገ-ወጥ መንገድ የተገጠሙ ቆጣሪዎች ተያዙ
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 22 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ገርጂ ጎሮ አካባቢ ልዩ ስሙ አሳማ እርባታ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ 17 ቆጣሪዎች በሕገ-ወጥ መንገድ ተገጥመው መገኘታቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ።
በሕገ-ወጥ መንገድ ተገጥመው የተገኙት ቆጣሪዎች ከእነፍጆታቸው አጠቃላይ ግምት ከ343 ሺህ ብር በላይ መሆኑን አገልግሎቱ ገልጿል።
የምሥራቅ አዲስ አበባ ዲስትሪክት ሕግ ክፍል ከፖሊስ ጋር በመተባበር በሕገ-ወጥ መንገድ የተገጠሙት ቆጣሪዎች፣ ኬብል እና ምሰሶ ተነሥተው ወደ ተቋሙ ገቢ እንዲሆኑ ማድረጉን አስታውቋል።
የአካባቢው ፖሊስ በሕገ-ወጥ ተግባሩ ላይ ምርመራ እያከናወነ እንደሚገኝ የአገልግሎቱ መረጃ ያመለክታል።