Fana: At a Speed of Life!

ዓለም አቀፉ የቴሌኮሙኒኬሽን ሕብረት ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን ድጋፍ እንዲያጠናከር ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፉ የቴሌኮሙኒኬሽን ሕብረት ለኢትዮጵያ የሚሰጠውን ድጋፍ ይበልጥ እንዲያጠናክር ተጠየቀ።

በጄኔቫ የኢትዮጵያ ቋሚ ተጠሪ አምባሳደር ፀጋአብ ከበበው ከዓለም አቀፉ የቴሌኮሙኬሽን ሕብረት ዋና ፀሃፊ ዶሬን ቦግዳን ማርቲን ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱ አምባሳደሩ ባለፉት አራት ዓመታት በኢትዮጵያ የቴሌኮም ዘርፉን ለነጻ የገበያ ወድድር ክፍት ለማድረግ የተከናወኑ ስራዎችን እና በእስካሁኑ ሂደት የተገኙ ውጤቶችን በተመለከተ ለዋና ፀሃፊዋ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ዓለም አቀፉ የቴሌኮሙኬሽን ሕብረት ለኢትዮጵያ እያደረገ ላለው ድጋፍ ምስጋና ያቀረቡት አምባሳደሩ ይኸው ድጋፍ ተጠናክሮ እዲቀጥል ጠይቀዋል።

በኢትዮጵያ የቴሌኮም ዘርፉን ለማዘመን የተወሰዱ የማሻያ ስራዎች አበረታች እና ውጤታማ ቢሆኑም የቴሌኮም ዘርፉ በዓለም ላይ እያስመዘገበ ካለው ፈጣን የቴክኖሎጂ እድገት አንጻር አሁንም እገዛ እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል፡፡

ህብረቱ የኢትዮጵያን የቴሌኮም ዘርፍ ለማመዘን በሚያደርገው እንቅስቃሴ ለዘርፉ ተቁዓማት የተለያዩ የቴክኒክ፥ የአቅም ግንባታ እና መሰል ደጋፎችን ሲያደርግ መቆየቱን ከጀኔቫ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕከተኛ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.