Fana: At a Speed of Life!

በፕሪምየር ሊጉ አዳማ ከተማ መቻልን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አዳማ ከተማ መቻልን 3 ለ 2 አሸነፈ፡፡

የ2015 የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ቀሪ የ17ኛ ሳምንት የጨዋታ መርሐ ግብር ዛሬ በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም መካሄድ ጀምሯል፡፡

በዚህም ዛሬ መቻል ከአዳማ ከተማ ጋር ጨዋታቸውን ያደረጉ ሲሆን÷በጨዋታው አዳማ ከተማ መቻልን 3 ለ 2 አሸንፏል፡፡

የአዳማ ከተማን ሁለት ጎሎች ዬሴፍ ታረቀኝ ሲያስቆጥር ቢኒያም አይተን አንዷን ጎል አስቆጥሯል፡፡

የመቻል ግቦች ደግሞ ሳሙኤል ሳሊሶ እና ግርማ ዲሳሳ አስቆጥረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.