ከለውጡ በኋላ የተገኘውን ድልና ስኬት ለማስቀጠል ያለመ የድጋፍ ሰልፍ በኦሮሚያ ክልል ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በመላው ኦሮሚያ ክልል ከለውጡ በኋላ የተገኘውን ድልና ስኬት ለማስቀጠል ያለመ የድጋፍ ሰልፍ ተካሂዷል፡፡
የድጋፍ ሰልፉ ተሳታፊዎች ከለውጡ በኋላ ባለፉት 5 ዓመታት በክልሉ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በማሕበራዊና በሌሎች ዘርፎች የተመዘገቡ ለውጦችን የሚያንጸባርቁ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል፡፡
በክልሉ ሁሉም ዞኖችና ከተማ አስተዳደሮች እየተካሄደ በሚገኘው የድጋፍ ሰልፍ ህዝቡ ድልና ስኬቶችን ለማስቀጠል ቁርጠኝነቱን በተለያዩ መፈክሮች አረጋግጧል፡፡
ሰልፈኞቹ የለውጡን ውጤቶች አጠናከረን እናስቀጥላለን፣ፀንፈኝነትን እንቃወማለን ፣ የህዳሴ ግድቡንና ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጀመሯቸውን የለውጡን ቱሩፋቶች ከጎናቸው ሆነን ከዳር እናደርሳለን፣ መጋቢት 24 የነጻነትነ የእኩልነት ሃውልት የተቀመጠበት ቀን ነው የሚሉና ሌሎች መልዕክቶችን አሰምተዋል፡፡
በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች በተካሄደው የድጋፍ ሰልፍ በርካታ ቁጥር ያላቸው ዜጎች ከለውጡ በኋላ የተገኘውን ድልና ስኬት ለማስቀጠል ቁርጠኝነታቸውን ገልጸዋል፡፡