Fana: At a Speed of Life!

በጅማ ከተማ ከለውጡ በኋላ የተገኘውን ድልና ስኬት ለማስቀጠል ያለመ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅማ ከተማና አካባቢው ከለውጡ በኋላ የተገኘውን ድልና ስኬት ለማስቀጠል ያለመ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው፡፡
 
በድጋፍ ሰልፉ የከተማዋ ነዋሪዎች ከመጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም ወዲህ በክልሉ የተመዘገቡ ድልና ስኬቶችን የሚያንጸባርቁ መልዕክቶችን እያስተላለፉ ነው፡፡
 
የድጋፍ ሰልፉ ተሳታፊዎች ከለውጡ በኋላ ባለፉት አምስት ዓመታት በክልሉ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በማሕበራዊና በሌሎች ዘርፎች የተመዘገቡ ለውጦችን የሚያስተጋቡ መፈክሮችን በማሰማት ላይ ይገኛሉ፡፡
 
በድጋፍ ሰልፉ የጅማ ከተማ እና የአካባቢው ነዋሪዎች እየተሳተፉ ነው፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.