Fana: At a Speed of Life!

በሸገር ከተማ ከለውጡ በኋላ የተገኘውን ድልና ስኬት ለማስቀጠል ያለመ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ከለውጡ በኋላ የተገኘውን ድልና ስኬት ለማስቀጠል ያለመ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው፡፡
 
በድጋፍ ሰልፉ የከተማዋ ነዋሪዎች ከመጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም ወዲህ በክልሉ የተመዘገቡ ድልና ስኬቶችን የሚያንጸባርቁ መልዕክቶችን እያስተላለፉ ነው፡፡
 
በድጋፍ ሰልፉ “መጋቢት 24 የመንግስትን ስርዓት በሴራና በሃይል የመቀየር አስተሳሰብን የዘጋ ታሪካዊ ቀን ነው፤ ሌብነትና ስንፍና የመጋቢት 24 ጠላቶች ናቸው፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጥበብ በተሞላበት አመራራቸው ስላሻገሩን እናመሰግናለን የሚሉና ሌሎች መፈክሮች እየተደመጡ ነው፡፡
ከለውጡ በኋላ ባለፉት አምስት ዓመታት በክልሉ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በማሕበራዊና በሌሎች ዘርፎች የተመዘገቡ ለውጦችን የሚያሳዩ መፈክሮችንም በማሰማት ላይ ናቸው፡፡
 
በድጋፉ ሰልፉ በሺህዎች የሚቆጠሩ የከተማው ነዋሪዎች እየተሳተፉ ነው፡፡
 
በሃብታሙ ተክለስላሴ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.