Fana: At a Speed of Life!

በነቀምቴ ከተማ ከለውጡ በኋላ የተገኙ ስኬቶችን የሚደግፍ ሰልፍ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በነቀምቴ ከተማ ከለውጡ በኋላ የተገኘውን ድልና ስኬት ለማስቀጠል ያለመ የድጋፍ ሰልፍ ተካሄደ ፡፡

የድጋፍ ሰልፉ ተሳታፊዎች ከመጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም ወዲህ በክልሉ የተመዘገቡ ድልና ስኬቶችን የሚያንጸባርቁ መልዕክቶች አስተላልፈዋል፡፡

በሰልፉ መጋቢት 24 የነጻነትነ የእኩልነት ሃውልት የተቀመጠበት ቀን ነው፣ ቀን ከሌት በሙሉ አቅም በመስራት ድህነትን ታሪክ እናደርጋለን፣ ሌብነትና ስንፍና የመጋቢት 24 ጠላቶች ናቸው የሚሉና ሌሎች መልዕክቶች ተላልፈዋል ፡፡

በድጋፍ ሰልፉ በርካታ ቁጥር ያላቸው የከተማዋ እና አካባቢው ነዋሪዎች ተሳትፈዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.