የሀገር ውስጥ ዜና

ከለውጡ በኋላ የተገኙ ድሎች እና ስኬቶችን አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል- የምስራቅ ቦረና እና ኢሉ አባቦር ዞኖች ነዋሪዎች

By Amele Demsew

April 02, 2023

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ቦረና እና ኢሉ አባቦር ዞኖች የተለያዩ አካባቢዎች ከለውጡ በኋላ የተገኘውን ድልና ስኬት ለማስቀጠል ያለመ የድጋፍ ሰልፍ ተካሂዷል፡፡

የድጋፍ ሰልፉ ተሳታፊዎች ከመጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም ወዲህ በክልሉ የተመዘገቡ ድልና ስኬቶችን የሚያንጸባርቁ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል፡፡

ከለውጡ በኋላ የተገኙ ድሎች እና ስኬቶችን አጠናክሮ ለማስቀጠል በትኩረት መስራት እንደሚገባ የድጋፍ ሰልፉ ተሳታፊዎች ተናግረዋል፡፡

በድጋፍ ሰልፉ በርካታ ቁጥር ያላቸው በዞኖቹ የተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ነዋሪዎች ተሳትፈዋል፡፡

#Ethiopia ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!