በለውጡ ያገኘናቸው ድሎችን በማስቀጠል ሁለንተናዊ ብልጽግናን እናረጋግጣለን-የቢሾፍቱና ሞጆ ከተሞች ነዋሪዎች
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቢሾፍቱ እና ሞጆ ከተሞች ከለውጡ በኋላ የተገኘውን ድልና ስኬት ለማስቀጠል ያለመ የድጋፍ ሰልፍ ተካሒዷል፡፡
በድጋፍ ሰልፉ የከተማዋ ነዋሪዎች ከመጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም ወዲህ በክልሉ የተመዘገቡ ድልና ስኬቶችን የሚያንጸባርቁ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል፡፡
ነዋሪዎቹ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በሳል አመራር እንደ ሀገር ለውጥ የተመዘገበበት ወቅት መሆኑን አንስተዋል፡፡
በመሰዋዕትነት የተገኘን ድል ሁላችንም በመተባባር ልጠብቀው ይገባል፤ በለውጡ ያገኘናቸው ድሎችን በማስቀጠል ሁለንተናዊ ብልጽግናን እናረጋግጣለን ሲሉም ተደምጠዋል፡፡