Fana: At a Speed of Life!

ጊዜያዊ ፈተናዎችን ሁሉ ተሻግረን የኢትዮጵያን ብልጽግና እናረጋግጣለን-ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጊዜያዊ ፈተናዎችን ሁሉ ተሻግረን የኢትዮጵያን ብልጽግና እና የሕዝቦቿን አንድነት እንደምናረጋግጥ የፀና እምነት አለን ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

ከንቲባ አዳነች በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷ መጋቢት 24 በኢትዮጵያ የለውጥ መሠረት የተጣለበት ቀን ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ለዚህም አዲስ አበባ ምሥክር ናት ያሉት ከንቲባዋ÷ በብዙ ፈተናዎች ውስጥ እምርታዎችን ማሳየት መቻሉን አንስተዋል።

ክብራችን ሕዝብን በፍትሐዊነት ማገልገል ነው፤ ዛሬም ፈተናዎች ቢበዙብንም የሕዝብን አደራ መቼም ቢሆን አንዘነጋም ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.