የረመዳን እና ዐቢይ ፆም የጋራ የፀሎት መርሐ ግብር ተከናወነ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የረመዳን እና ዐቢይ ፆም የጋራ የፀሎት መርሐ ግብር ተከናወነ፡፡
መርሐ ግብሩ በአዲስ አበባ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት ቅጥር ጊቢ ውስጥ ነው የተከናወነው።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመርሐ ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር፥ የጋራ የፀሎት ሥነ ስርዓቱ የዐቢይና የረመዳን ፆም አንድ ላይ በገጠሙበት እንዲሁም የለውጥ መሰረት በተጣለባት መጋቢት 24 መሆኑ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል።
ኢትዮጵያውያን ያሉንን የጋራ እሴቶች ይበልጥ ለማጠናከር ቤተዕምነቶች ስለሠላም አበክረው እንዲሠሩ ጠይቀዋል።
እንደሀገር ከሚያለያየን ይልቅ አንድ የሚያደርገን ይበልጣል፤ ለዚህም ይህ የጋራ ማዕድ ተዘጋጅቷል ብለዋል።
በመርሐ ግብሩ ላይ ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼህ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ እና የሁሉም ቤተ ዕምነት አባቶች እና ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
በወንድሙ አዱኛ
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!