Fana: At a Speed of Life!

ከሙስና ጋር በተገናኙ 52 ጥቆማዎች ላይ ምርመራ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የፀረ ሙስና ኮሚቴ ከሙስና ጋር በተያያዘ 52 ጥቆማዎችን ተቀብሎ ምርመራ መጀመሩን አስታወቀ፡፡

የክልሉ ፍትሕ ቢሮ ኃላፊ እና የኮሚቴው ሰብሳቢ ሰዒድ ባበክር በሰጡት መግለጫ÷ በ44 ጥቆማዎች 93 ተጠርጣሪዎች ተይዘው ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን አንስተዋል፡፡

የ45 ሚሊየን ብር ጉዳት መድረሱ በምርመራ ተረጋግጧል ያሉት አቶ ሰዒድ÷ ከተመዘበረው ገንዘብም ከ463 ሺህ ብር በላይ ለመንግስት ተመላሽ መደረጉን ተናግረዋል፡፡

በሕገ ወጥ መንገድ የተያዘ ከ99 ሺህ ካሬ ሜትር በላይ መሬት በፍርድ ቤት ታግዷል ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ የሰባት መዝገቦች ምርመራ መጠናቀቁን ጠቁመዋል፡፡

በአንድ የሙስና መዝገብ በ8 ግለሰቦች ላይ ክስ የቀረበ መሆኑንና በገንዘብ ሲተመን ከ22 ሚሊየን 468 ሺህ በላይ ብር ጉዳት መድረሱን አመላክተዋል፡፡

ሕብረተሰቡ የፀረሙስና ትግሉን ውጤታማ ለማድረግ ትክክለኛ ጥቆማዎችን ከመስጠት ጀምሮ እስከ ምስክርነት ተሣትፎውን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.