Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያና እንግሊዝ ፓርላማዎች ግንኙነታቸውን ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚሰሩ አስታወቁ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያና እንግሊዝ ፓርላማዎች የእርስ በርስ ግንኙነታቸውን ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚሰሩ አስታወቁ፡፡

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዲማ ነገዎ(ዶ/ር) የእንግሊዝ ፓርላማ ልዑካን ቡድንን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

በውይይታቸውም÷ የሁለቱ አገሮች የፓርላማ ለፓርላማ ግንኙነታቸውን በሚያጠናክሩባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

ዲማ ነገዎ(ዶ/ር) በውይይቱ÷ አገራቱ ያላቸውን ወዳጅነት በፓርላማ ለፓርላማ ግንኙነት ይበልጥ በማጠናከር ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገር ይገባል ብለዋል፡፡

ሰብሳቢው ይህን እውን ለማድረግ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የበኩሉን ድርሻ  ይወጣል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የእንግሊዝ ፓርላማ አባልና የልዑክ ቡድኑ መሪ ሮቢን ሚላር በበኩላቸው÷ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ፓርላማ ጋር ያላትን ግንኙነት ማጠናከር እንደምትሻ ገልጸዋል።

በዚህም በቀጣይ ፓርላማዎቹ በትብብር የሚሰሩበትን ዕድል በመፍጠር ግንኙነታቸውን የበለጠ ለማጠናከር እንደሚሰራ ተናግረዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.