የዓለም ጤና ድርጅት የሰዎችን ህይወት ማዳን ላይ ትኩረት ያደርጋል- ዶክተር ቴድሮስ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 7፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የዓለም ጤና ድርጅት የሰዎችን ህይወት ማዳን እና የኮሮና ቫይረስን መከላከል እንዲሁም መቆጣጠር ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ ዶክተር ቴድሮስ ገለፁ።
የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ የሚባክን ሰዓት የለም ሲሉ በትዊተር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።
There is no time to waste. @WHO’s singular focus is on working to serve all people to save lives and stop the #COVID19 pandemic. https://t.co/08xlv7HLC4
— Tedros Adhanom Ghebreyesus (@DrTedros) April 15, 2020
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሀገራቸው ለድርጅቱ የምታደርገውን ዓመታዊ መዋጮ እንድታቋርጥ ውሳኔ ማሳለፋቸውን ተከትሎ የተለያዩ ሀገራት አስተያየት እና ተቃውሟቸውን እያሰሙ ይገኛል።
ቻይናም ዶናልድ ትራምፕ ለዓለም ጤና ድርጅት አሜሪካ የምትሰጠውን ድጋፍ ማቋረጧን በመቃወም ለድርጅቱ የምታደርገውን ድጋፍ እንደምትቀጥል ገልፃለች።
የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን በተመለከተ ዋነኛ የመረጃ ምንጭ የሆነው የጆን ሆፕኪንስም ውሳኔውን በመቃወም በዚህ ወረርሽኝ ወቅት ውሳኔው መጥፎ መልዕክትን ያስተላለፈ ነው ብሏል።
የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ ሃላፊ ጆሴፍ ቦሬል በበኩላቸው 27ቱ የህብረቱ አባል ሀገራት የድጋፉ መቋረጥ በእጅጉ እንዳሳዘናቸው ገልፀዋል።
ድርጅቱ በአሁኑ ወቅት የኮሮና ወረርሽኝን ለመቆጣጠር ከምንጊዜም በላይ የሚያስፈልግበት ወቅት መሆኑን ተናግረዋል።
በተመሳሳይ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሙሳ ፋቂ ማህማት፣ የማይክሮሶፍት ኩባንያ መስራችና ዋና ስራ አስፈፃሚ ቢል ጌትስ እና ሌሎች ግለሰቦች እንዲም ተቋማት የዶናልድ ትራምፕን ውሳኔን ተቃውመዋል።
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision