Fana: At a Speed of Life!

የታላቁ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅ የቀጣናውን ሀገራት ግንኙነት ይበልጥ ያጠናክራል – ምሁራን

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የታላቁ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅ የቀጣናውን ሀገራት ግንኙነት ይበልጥ እንደሚያጠናክር ምሁራን ገለጹ፡፡

በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደርና ልማት ኢንስቲትዩትመምህር መሃመድ አሊ (ዶ/ር) ÷ግድቡ በጋራ ለማልማት ቆርጠው የተነሱ ህዝቦች የተባበረ ክንዳቸውን ያሳዩበት ነው ብለዋል፡፡

የታላቁ ሕዳሴ ግድብ በራስ አቅም የሚሰራና የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦር ችግር ላለባቸው በርካታ ዜጎች ተስፋ መሆኑንም አውስተዋል፡፡

ግድቡ ከፍጻሜው ሲደርስም የቀጠናውን ግንኙነት የሚያጠናክር እና በፖለቲካም ይሁን በኢኮኖሚው ዘርፍ የሚሰጠው ጥቅም የጎላ መሆኑን አፅንኦት ሰጥተዋል፡፡

እየተገነባ ያለው ግድብ ሲጠናቀቅ ጎርፍን ከመከላከል ጀምሮ የሃይል አቅርቦትን እስከማስፋፋት ድረስ በርካታ ጥቅሞችን እንዳሉትም ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል ፡፡

የቀድሞው የሱዳን ዲፕሎማትና ጋዜጠኛ መኪ አል መግርቢ በበኩላቸው ÷የሱዳንንና የኢትዮጵያ ህዝቦች ከአንድ ምንጭ የሚጠጡ፣ በባህልና ወግ የተሳሰሩ ወንድማማች ህዝቦች ናቸው ብለዋል፡፡

ግድቡ የአፍሪካ ቀንድና የተፋሰሱን ሀገራት ትስስር የሚያበረታ በመሆኑ ከአሉታዊ ሃሳቦች ይልቅ በአዎንታዊ ጉዳዮች ላይ ማተኮር ይገባልም ነው ያሉት፡፡

ከአሉታዊ ሃሳቦች ይልቅ ለቀጣናው ህዝቦች ትስስር እናተጠቃሚነት ቅድሚያ መስጠት እንደሚገባም አስረድተዋል፡፡

ምሁራኑ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ለቀጣናው የሚያመጣውን የሰላምና ልማት ትሩፋት ለመጠቀም ሀገራት በጋራ መስራት ይገባቸዋል ብለዋል፡፡

በሃይማኖት ወንድራድ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.