ዓለምአቀፋዊ ዜና

የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ፍርድ ቤት ቀረቡ

By Amele Demsew

April 04, 2023

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዛሬው ዕለት በኒውዮርክ ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡

በአሜሪካ ታሪክ በወንጀል የተከሰሱ የመጀመሪያው የቀድሞ ፕሬዚዳንት የሆኑት ዶናልድ ትራምፕ÷በአሁኑ ስዓትም የቀረበባቸው ክስ ለመስማት ኒዮርክ በሚገኘው ፍርድቤት ተገኝተዋል፡፡

ዶናልድ ትራምፕ ከወሲብ ፊልም ተዋናይት ስቶርሚ ዳንኤልስን ጋር የፈጸሙት ጾታዊ ግንኙነት ይፋ እንዳይሆን ዝም ለማሰኘት 130 ሺህ ዶላር ከፍለዋል በሚል ነው ለክስ የተዳረጉት፡፡

ትራምፕ በፈረንጆቹ 2016 በአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ አሸናፊ ከመሆናቸው ቀደም ብሎ ለግለሰቧ የከፈሉት ገንዘብ አለ በሚል በኒውዮርክ ጠበቆች ምርመራ ሲደረግ መቆየቱ ተጠቁሟል፡፡

ምርመራው ትራምፕ ከቀድሞዋ የወሲብ ፊልም ተዋናይት ጋር የፈጸሙት ጾታዊ ግንኙነት ይፋ እንዳይሆን ገንዘብ ከፍለዋል በሚል ሲካሄድ መቆየቱን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

#Ethiopia ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!