Fana: At a Speed of Life!

ፈረንሳይ እና የአውሮፓ ኅብረት በሩሲያ – ዩክሬን ጉዳይ ላይ ከቻይና ጋር ሊመክሩ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛሬው ዕለት ፈረንሳይ እና የአውሮፓ ኅብረት ኮሚሽን በዩክሬን ጉዳይ ላይ ከቻይና ጋር ሊመክሩ ነው።

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን እና የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኡርሱላ ቮን ዴር ሌየን ለሶስት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ወደ ቻይና አቅንተዋል።

ከዛሬ ጀምሮ በሚኖራቸው ቆይታም ከቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ጋር በሩሲያ – ዩክሬን ጉዳይ ላይ ይመክራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ አልጀዚራ ዘግቧል።

በተለይም ማክሮን ቻይና በጉዳዩ ላይ ከሩሲያ ጎን እንዳትወግን የማግባባት ስራ ይሰራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ነው ዘገባው ያመላከተው።

ቻይና በሩሲያ ጉዳይ ጣልቃ የመግባት ፍላጎት ባይኖራትም የፕሬዚዳንት ቭላድሜር ፑቲን የቅርብ ወዳጅ እንደመሆኗ መጠን ከውይይቱ አንዳች ተሥፋ ሠጪ ውጤት ሊገኝ ይችላል እየተባለ ነው፡፡

ኢማኑዔል ማክሮን ከ50 በላይ ሥራ አሥፈጻሚ ልዑካንን በጉብኝታቸው መርሐ-ግብር ላይ ማካተታቸውም ተጠቁሟል፡፡

ከወቅታዊው የዩክሬን እና የሩሲያ ጉዳይ በዘለለ በኢኮኖሚያዊ እና በንግድ ጉዳዮች ላይ ከቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ጋር ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት በቻይና የፈረንሳይን የንግድ ማኅበረሰብ አባላትን እንደሚያገኙም ተነግሯል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.