የሀገር ውስጥ ዜና

የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ዝቅተኛ የተከፈለ ካፒታል መጠን ወደ 75 ሚሊየን አደገ

By Alemayehu Geremew

April 05, 2023

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማትን ዝቅተኛ የተከፈለ ካፒታል መጠን ከ50 ሚሊየን ወደ 75 ሚሊየን አሳደገ።

ባንኩ ከዚህ ውሳኔ የደረሰው ወቅታዊውን ሀገራዊ የማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታ እና የተቋማቱን አቅም አገናዝቦ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በኢትዮጵያ የተረጋጋ የኢኮኖሚ ዕድገት መኖሩ እንዲሁም እየጨመረ የመጣው የብድር ፍላጎት ለውሳኔው በምክንያትነት መነሳቱን የባንኩ መረጃ ያመላክታል፡፡

እንዲሁም በዘመናዊው የፋይናንስ የመሠረተ ልማት እና አቅርቦት ዘርፍ መዋዕለነዋይ ለማፍሰስ እያደገ የመጣው ፍላጎት በምክንያትነት ተጠቅሰዋል፡፡

ውሳኔው ከፈረንጆቹ ጥር 16 ቀን 2023 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ መደረጉም ነው የተመለከተው፡፡