Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች ከፍል ውሃ አካባቢ ለልማትና ከወንዝ ዳርቻ አካባቢዎች ለተነሱ ነዋሪዎች ቤቶችን ያስተላልፋሉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከፍል ውሃ አካባቢ ለልማት እና ከወንዝ ዳርቻ አካባቢዎች ለተነሱ ነዋሪዎች በዛሬው ዕለት ቤቶችን እንደሚያስላልፉ ተገለጸ::

በዚህም መሰረት:-

1. 200 ቤቶች ለልማት እና በወንዝ ዳርቻ ልማት ከጉለሌ ፣ አራዳ እና ልደታ ለተነሱ ነዋሪዎች ይተላለፋሉ፤

2. 5ነጥብ 6 ሄክታር መሬት ለልማት ለተነሱ ነዋሪዎች የተዘጋጀ ሲሆን 1ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ካሳ ለነዚሁ ተነሺዎች ተከፍሏል፤

3. ኮንዶሚኒየም ቤት ተመድቦላቸው የቤቱ ግንባታ ተጠናቅቆ ቤታቸው እስኪገቡ የአምስት ወር የቤት ኪራይ በአጠቃላይ 36ነጥብ 6 ሚሊየን ብር የቤት ኪራይ ክፍያ መፈጸሙንም ከከንቲባ ጽህፈት ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ በመግለጫው፥ ከተማችን የምታፈናቅል ሳትሆን ሁሉንም ነዋሪዎች እኩል ተጠቃሚ የምታደርግ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን በመደገፍ የተሻለ ጤናማ የመኖሪያ አካባቢን በመፍጠር ላይ የምትገኝ ከተማ ናት” ብሏል።

“ለነዋሪዎቻችን በቂ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ያለው ምቹ የመኖሪያ አካባቢን በመገንባት፣ የወንዝ ዳርቻዎችን በማልማት፣ የቱሪስት መተላለፊያ ሳትሆን የቱሪስት መዳረሻ የሆነች ከተማ ለመገንባት የተጀመረው ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል” ብሏል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.