ዓለምአቀፋዊ ዜና

ፕሬዚዳንት ፑቲን የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች በሩሲያ አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ እንዲሳተፉ ጋበዙ

By Mikias Ayele

April 06, 2023

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭድሚር ፑቲን የአፍሪካ መሪዎች በሴንት ፒተርስበርግ በሚካሄደው የሩሲያ አፍሪካ ጉባኤ እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ፑቲን በጣም አስፈላጊ ሲሉ ለገለፁት የሩሲያ አፍሪከ የመሪዎች ጉባኤ ሩሲያ በቂ ቅድመ ዝግጅት እያደረገች መሆኑን አንስተዋል፡፡

የአፍሪካ ሀገራት መሪዎችን እና የቀጣናዊ ድርጅቶች ሃላፊዎች የሚሳተፉ በመሆኑ ከወዲሁ ደስተኞች ነን ማለታቸውን ስፑትኒክ ዘግቧል፡፡

የሩሲያ አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ በመጭው ሀምሌ ወር በሩሲያ ሴንት ፒተርስበርግ ከተማ ይካሄዳል፡፡