የሀገር ውስጥ ዜና

በአቶ አደም ፋራህ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑክ ከጅቡቲ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያየ

By Melaku Gedif

April 06, 2023

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በብልጽግና ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑክ ከጅቡቲ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጌሌ ጋር ተወያይቷል፡፡

በውይይታቸውም ሀገራቱ ያላቸውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ ማሳደግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡

ኢትዮጵያ እና ጅቡቲ በዲፕሎማሲ፣ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና በማህበራዊ ዘርፎች ላይ ያላቸውን ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚሰሩም ተገልጿል፡፡

ልዑካኑ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተላከን ደብዳቤ ለጅቡቲ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጌሌ ማድረሳቸውን የኤምባሲው መረጃ ያመላክታል፡፡

በብልጽግና ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑክ በጅቡቲ የስራ ጉብኝት እያደረገ መሆኑ ይታወቃል፡፡