Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ ሙስሊም ወገኖች የረመዳን ኢፍጣር ማዕድ አጋሩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአዲስ አበባ በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ ሙስሊም ወገኖች የረመዳን ኢፍጣር ማዕድ አጋሩ።

በኢፍጣር ማዕድ ማጋራት መርሐግብሩ ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት፣ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ስራ አስፈጻሚ አባላት፣ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም በዝቅተኛ ገቢ የሚተዳደሩ ሙስሊም ወገኖች ተገኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ባለፈው ሳምንት የመንግስትን የስድስት ወራት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡበት ወቅት ሕብረተሰቡ የረመዳን ጾምንና መጪውን የትንሳኤ በዓል ምክንያት በማድረግ አቅም ለሌላቸው ዜጎች ማዕድ እንዲያጋሩ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወቃል።

ይህንን ተከትሎም በአዲስ አበባና በሌሎች የአገሪቱ አካባቢዎች የማዕድ ማጋራትና ሌሎች የበጎነት ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከዚህ ቀደም ከሳዑዲ ለተመለሱ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም በኢትዮጵያ ለሚኖሩ የየመንና የሶሪያ ስደተኞች የኢፍጣር ማዕድ ማጋራታቸው ይታወሳል።

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.