Fana: At a Speed of Life!

በአሜሪካ የሚኖሩ ሁለት እህታማማቾች 7ሺህ መጻሕፍት ለአብርሆት ቤተ መጻሕፍት ለገሱ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ የሚኖሩ ሁለት እህታማማቾች በትውልድ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ለአብርሆት ቤተ መጻሕፍት ያሰባሰቡትን 7ሺህ መጻሕፍት ለኢትዮጵያ ኤምባሲ አስረክበዋል።

ወ/ሮ አያንቱ አበበ በልጆቻቸው በኩል የተሰበሰቡትን መጻሕፍትን ለኤምባሲው አስረክበዋል።

ልጆቻቸው ከኢትዮጵያ ጋር ጥብቅ ትስስር እንዲኖራቸው ለማድረግና የበጎ ስራ አርዓያ እንዲሆኑ ይህ መጻሕፍትን የማሰባሰብ ስራ መጀመሩን አውስተዋል።

የተለገሱት መጻሕፍት በኢትዮጵያ የንባብ ባህል፣ እንዲዳብር ቤተ መጻሕፍት የተሟላ አቅርቦት እንዲኖራቸው ለማገዝ ነው ብለዋል።

የተለገሱት መጻሕፍት የቋንቋ፣ ስነ ሕወይት፣ ታሪክ፣ ሒሳብ፣ ምርመርና ሌሎች ጠቃሚ ዘርፎች ላይ ያተኮሩ እንደሆኑ ሁለቱ እህታማማቾች ገልጸዋል።

በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስለሺ በቀለ (ዶ/ር ኢ/ር)፣ ይህን መሰል ትውልድን የሚያንጹ መጻሕፍት በመለገስ ለተደረገው አርዓያነት ያለው ስራ ምስጋና አቅርበዋል።

መጻሕፍቱም ከሌሎች መሰል የዳያስፖራ ወገኖች ከለገሷቸው ጋር በመሆን ለአብርሆት ቤተ መጻሕፍት የሚላኩ መሆናቸውን በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.