Fana: At a Speed of Life!

አቶ ሽመልስ አብዲሳ ከብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 29 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ከብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይቱ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወሉ አብዲን ጨምሮ የክልሉ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

በመድረኩ ላይ ርዕሰ መስተዳድሩ እንደተናገሩት የክልሉ መንግስት በክልሉ የሚገኙ የቀድሞ ሰራዊት አባላትን መልሶ የማቋቋም እና የተጎዱ የማህበረሰብ ክፍሎችን ለመደገፍ መርሐ ግብር ጀምሯል።

የክልሉ መንግስት ከኮሚሽኑ ጋር በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆኑንም አረጋግጠዋል።

አምባሳደር ተሾማ ቶጋ በበኩላቸው የኮሚሽኑ ዋና አላማ ለሀገርና ለህዝብ ሀገራዊ አገልግሎት የሰጡ እና በጦርነት መስዋዕትነት የከፈሉ የቀድሞ ሰራዊት አባላትን መልሶ ማቋቋም ነው ብለዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.