Ljubljana, DZ. Nova ministrica za zunanje zadeve Tanja Fajon.

የሀገር ውስጥ ዜና

በስሎቬኒያ የውጭና የአውሮፓ ጉዳዮች ሚኒስትር የተመራ ልዑክ ለስራ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ ይመጣል

By Alemayehu Geremew

April 07, 2023

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 29 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በስሎቬኒያ የውጭና የአውሮፓ ጉዳዮች ሚኒስትር ታኒያ ፋየን የተመራ ልዑክ በኢትዮጵያ የሦስት ቀናት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት እንደሚያደርግ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ እንደሚያመላክተው ሚኒስትሯ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡት ከከፍተኛ የልዑካን ቡድናቸው ጋር ነው፡፡

በኢትዮጵያ የሚኖራቸው የሥራ ቆይታም ከፊታችን ሚያዚያ 3 እስከ 5 ቀን 2015 ዓ.ም መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ልዑካኑ በቆይታቸውም ከኢትዮጵያ መንግስት የተለያዩ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ጋር ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡