Fana: At a Speed of Life!

በዩኒቨርሲቲዎች የአስተዳደር ነፃነት አለመኖሩ በእድገታቸው ላይ ተፅዕኖ ፈጥሯል-ፕ/ር ጣሰው ወልደሃና

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዩኒቨርሲቲዎች የአስተዳደር ነፃነት አለመኖሩ በእድገታቸው ላይ ተፅዕኖ ፈጥሯል ሲሉ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ጣሰው ወልደሃና (ፕ/ር) ተናገሩ።

የዩኒቨርሲቲዎችን እራስ ገዝ መሆን በተመለከተ በቢሾፍቱ ከተማ ውይይት ተደርጓል፡፡

በውይይቱ ንግግር ያደረጉት ፕሬዚዳንቱ በዚህ ወቅት ዩኒቨርሲቲዎች ላለፉት አመታት የአካዳሚክ ነፃነት እንደ ችግር የሚታይ ባይሆንም የአስተዳደር ነፃነት ግን ለዩኒቨርሲቲዎቹ እድገት ማነቆ ሆኖ ቆይቷል ብለዋል።

በመሆኑም የዩኒቨርሲቲዎች እራስ ገዝ መሆን አስፈላጊ መሆኑን በመጥቀስ፥ በሀገር ጉዳይ ላይ ሀሳብ አፍላቂ፣ ተመራማሪ፣ በዓለም አቀፍ ታዋቂ ዩኒቨርሲቲዎችን ለመፍጠር ወሳኝ መሆኑንም ተናግረዋል።

የዩኒቨርሲቲዎች እራስ ገዝ መሆን በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቶ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተላከ ሲሆን የተደረገው  ውይይትም በረቂቅ አዋጁ ላይ ግብዓት ለመሰብሰብ ነው ተብሏል።

በውይይቱ የዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንቶችና የሚመለከታቸው አካላት ተሳትፈዋል፡፡

በታሪኩ ለገሰ

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.