Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የፋና ላምሮት ምዕራፍ 13 የድምፃውያን ውድድር ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በፋና ቴሌቪዥን የሚዘጋጀውና ተወዳጁ የፋና ላምሮት የባለ ተሰጥኦ ድምጻውያን ውድድር 13ኛ ምዕራፍ በዛሬው ዕለት ተጀምሯል።

ፋና ላምሮት ከአዳዲስ ተወዳዳሪዎችና ባለተሰጥኦዎች ጋር በቀጥታ ስርጭት የጀመረ ሲሆን፥ በሁለት ምድብ የተከፈሉ 12 ተወዳዳሪዎች በድምጽ ውድድር ይሳተፋሉ።

ለዘጠኝ ሳምንታት የድምጻውያን ውድድር መጨረሻ የሚቀሩ አራት የምዕራፉ ተፋላሚዎችን ተሸላሚ ያደርጋል፡፡

የውድድሩ ተመልካቾችም በቀጥታ ስርጭት ወደ 8222 አጭር የፅሁፍ መልዕክት በመላክ ለሚደግፉት ተወዳዳሪ ድምፅ መስጠት ይችላሉ።

ከዚህ ቀደም ፋና ላምሮት በ12 ምዕራፎች መካሄዱ ይታወሳል።

Exit mobile version