አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ቡና እና ባሕርዳር ከተማ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸነፉ፡፡
በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 18ኛ ሣምንት ጨዋታ በአዳማ ሣይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ተካሂዷል፡፡
በዚህም 9፡00 ላይ በተካሔደው ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና ወልቂጤ ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡
ለቡና የማሸነፊያዋን ጎል ብሩክ በየነ በሁለተኛው አጋማሽ አስቆጥሯል፡፡
በሌላ በኩል ምሽት 12፡00 ላይ በተካሄደው ጨዋታ የጣና ሞገዶቹ ዐጼዎቹን 2 ለ 1 ማሸፍ ችለዋል፡፡
የባሕርዳር ከተማን ጎሎች ያሬድ ባዬ እና አለልኝ አዘነ አስቆጥረዋል፡፡
የፋሲል ከነማን ብቸኛ ጎል ደግሞ ታፈሰ ሰሎሞን ነው ያስቆጠረው፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!