Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ የህዝብን ጥያቄን የሚመልሱ ሜጋ ፕሮጀክቶች እየተገነቡ ነው -ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በመዲናዋ የሕዝብን ጥያቄ የሚመልሱ ሜጋ ፕሮጀክቶች እየተገነቡ እንደሆነ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

ከንቲባ አዳነች ከከተማ አስተዳደሩ አመራሮች ጋር በመሆን በመዲናዋ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች እየተገነቡ ያሉ ፕሮጀክቶች የደረሱበትን ደረጃ ተመልክተዋል።

የኮልፌ ጠቅላላ ሆስፒታል፣ የኮልፌ እና የአያት የግብርና ምርቶች የገበያ ማዕከላት፣የለቡ ተሻጋሪ መንገድን ጨምሮ የተለያዩ የመንገድ እና የድልድይ ፕሮጀክቶች፣ የኢንዱስትሪ ክላስተር እና የአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ ማዕከል ከተጎበኙ ፕሮጀክቶች መካከል ይጠቀሳሉ።

በመዲናዋ የህዝብ ጥያቄ የነበሩ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ለመገንባት በተያዘው ዓመት በከተማ አስተዳደሩ 56 ቢሊየን ብር ተመድቦ ትልልቅ ፕሮጀክቶች እየተሰሩ መሆኑን ከንቲባዋ አንስተዋል።

አሁን ላይ ከተመደበው በጀት 4 ቢሊየን ብር የበጀት ጭማሬ ተደርጎ በአጠቃለይ ወደ 60 ቢሊየን ብር ለዚሁ አላማ ለማዋል መመደቡንም ገልፀዋል።

የተጀመሩ ፕሮጀክቶች ሲጠናቀቁ የማህበረሰቡን ዘርፈ ብዙ ጥያቄዎች ይፈታሉ ተብሎ ይታመናልም ነው ያሉት ከንቲባዋ ፡፡

ፕሮጀክቶች አሁን ያሉበት ደረጃ የሚበረታታ መሆኑን ገልፀው÷ ሁሉም በጊዜ ተጠናቅቀው ለታለመላቸው አላማ እንዲውሉ ይሰራል ብለዋል፡፡

በሳሙኤል ወርቃየሁ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.