Fana: At a Speed of Life!

አለሙ ስሜ (ዶ/ር) በህዝብ ትራንስፖርት ተርሚናሎች የሚሰጡ አገልግሎቶችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትሩ አለሙ ስሜ (ዶ/ር) በህዝብ ትራንስፖርት ተርሚናሎች የሚሰጡ አገልግሎቶችን ጎበኙ፡፡

ሚኒስትሩ በዛሬው እለት በላምበረት እና በአዲስ ከተማ ህዝብ ትራንስፖርት ተርሚናሎችን ነው በትራንስፖርት ስምሪት መስጫ ሰአት ተገኝተው የሚሰጡ አገልግሎቶችን የጎበኙት፡፡

በጉብኝታቸው÷ በተርሚናሎቹ የሚሰጡ አገልግሎቶችን የተመለከቱ ሲሆን÷ የስምሪት አሰጣጣ ስርዓትን፣ የተሳፋሪዎችን አያያዝ፣ የትራንስፖርት ታሪፍ ተግባራዊነትን እና አገልግሎቶች ህብረተሰቡን በሚመጥን መልኩ አገልግሎት እየተሰጡ መሆኑን ፈትሸዋል ነው የተባለው፡፡

የሚሰጡ አገልግሎቶችን በተመለከተ በተርሚናሎች ውስጥ በተለያዩ ዘርፍ አገልግሎት የሚሰጡ አደረጃጀቶችን እና ተሳፋሪዎችንም ማነጋገራቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ሚኒስትሩ በጉብኝታቸው ያስተዋሏቸው የአገልግሎት አሰጣጥ ክፍተቶች በአስቸኳይ ማስተካከያ እንዲደረግባቸው ያሳሰቡ ሲሆን÷ በቀጣይም በተርሚናሎች የሚሰጠው የህዝብ ትራንስፖርት ስምሪት አገልግሎት በጥብቅ ክትትል እንደሚመራ ገልፀዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.