Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል 7 ነጥብ 8 ሚሊየን ሕዝብን ተጠቃሚ የሚያደርግ የምግብ ሥርዓት ማጠናከሪያ መርኃ ግብር ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል 7 ነጥብ 8 ሚሊየን ሕዝብን ተጠቃሚ የሚያደርግ የምግብ ሥርዓት ማጠናከሪያ መርኃ ግብር በይፋ ተጀምሯል፡፡

በኢትዮጵያ ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና የሕዝቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ ያለመ ሦስተኛው ምዕራፍ የምግብ ሥርዓት ማጠናከሪያ መርኃ ግብር ጥር ወር ጀምሮ ተግባራዊ መደረግ ጀምሯል፡፡

የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ ኃይለማርያም ከፍያለው (ዶ/ር) በዚሁ ጊዜ እንዳሉት የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት የተለያዩ የልማት መርኃ ግብሮች ተግባራዊ እየተደረጉ ይገኛሉ።

ከእነዚህ መካከል አንዱ የኢትዮጵያ የምግብ ሥርዓት መርኃ ግብር መሆኑን ያነሱት ቢሮ ኃላፊው ለሚቀጥሉት 7 ዓመታት ተግባራዊ እንደሚደረግ ገልጸዋል።

በክልሉ በዘጠኝ ዞኖችና በ48 ወረዳዎች የሚተገበረው የምግብ ሥርዓት ማጠናከሪያ መርኃ ግብር 7 ነጥብ 8 ሚሊየን ሕዝብን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።

የምግብ ሥርዓት ማጠናከሪያ መርኃ ግብሩ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ሲሆን 5 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር እንደተመደበለትም ነው የተናገሩት።

ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የሕዝቡን የምግብ ዋስትና ክፍተት ለመሙላት በየደረጃው የተዋቀረው አስፈጻሚ አካል በቁርጠኝነት መሥራት እንዳለበት መናገራቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.