በናይጄሪያ አንድ የህክምና ባለሙያ በኮሮናቫይረስ ህይወቱ አለፈ
አዲስ አበባ፣ሚያዚያ 8፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በናይጄሪያ አንድ የህክምና ባለሙያ በኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) ምክንያት ህይወቱ ማለፉ ተሰምቷል።
በናይጄሪያ በበኮሮናቫይረስ ምክንያት በህክምና ባለሙያ ላይ የደረሰው ህልፈት በአፍሪካ የመጀመሪያው ሲሆን፥ ለህልፈት የተዳረገው ዶክተር በግሉ ክሊኒክ ውስጥ በቫይረሱ የተያዘውን ታማሚ በሚያክምበት ወቅት በመያዙ ነው ተብሏል፡፡
ዶክተሩ ባሳለፍነው ሰኞ ዕለት ሌጎስ ዩኒቨርስቲ የማስተማሪያ ሆስፒታል ለህክምና ገብቶ የነበረ ሲሆን፥ በወቅቱ ከባድ የህመም ምልክቶች ይታዩበት ነበር ተብሏል።
የናይጄሪያ የህክምና ማህበር ዶክተር ቹጎቦ ኢመካ አርብ እለት በኮሮና ቫረስ ለህልፈት የተዳረገን ታማሚ በሚያክምበት ወቅት ለቫይረሱ መጋለጡን አስታውቋል።
በከጆሮና ቫይረስ ህይወቱ ያለፈው የ51 ዓመቱ ዶክተር የአስም በሽታ እንደነበረበት የህክምና ማህበሩን ጠቅሶ የቫንጋርድ ጋዜጣ ማስነበቡ ተነግሯል።
ምንጭ፦ ቢ.ቢ.ሲ
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!