Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን ከስሎቬኒያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከስሎቬኒያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ታኒያ ፋየን ጋር ተወያዩ፡፡

በውይይታቸውም በሁለትዮሽና በባለብዙ ወገን ግንኙነት ላይ መክረዋል፡፡

በውይይቱ ላይ እንደተገለጸው÷ስሎቬኒያ ከኢትዮጵያ ጋር በተለያየ መስክ በትብብር ለመስራት ፍላጎት አላት፡፡

ሀገራቱ በኢኮኖሚ፣ በግብርና፣ በፋርማሲቲካል፣ በውኃና ቱሪዝም ላይ በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለሰ አለም ገልጸዋል፡፡

ስሎቬኒያ በንብ ማነብ በዓለም ስመጥር ስለሆነች በመስኩ ከኢትዮጵያ ጋር ለመስራት ስምምነት ላይ መደረሱን ጠቅሶ ኢዜአ ዘግቧል፡፡

እንዲሁም ስሎቬኒ በኢትዮጵያ ኤምባሲ ልትከፍት ስለመሆኗም ነው የተመለከተው፡፡

አቶ ደመቀ መኮንን ኢትዮጵያና ስሎቬኒያ ታሪካዊ ወዳጅነት ያላቸው ሀገራት መሆናቸውን ጠቅሰው÷ በኢትዮጵያ እየተከናወነ ስላለው የሰላም ሂደት ማብራሪያ መስጠታቸውን አምባሳደር መለሰ ዓለም ተናግረዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.