Fana: At a Speed of Life!

የቄራዎች ድርጅት ከ5 ሺህ በላይ የዕርድ እንስሳት አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በመጪው የትንሳዔ በዓል ከ5 ሺህ በላይ የዕርድ እንስሳት አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅት ማጠናቀቁን የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ገለጸ፡፡

የድርጅቱ የሕዝብ ግንኙነት አገልግሎት ኃላፊ አታክልቲ ገብረሚካኤል ለትንሳዔ ከ5 ሺህ በላይ የዕርድ እንስሳት እንደሚቀርቡ ጠቁመው የተሳለጠ አገልግሎት ለመስጠትም ዝግጅት መጠናቀቁን አረጋግጠዋል፡፡

በዚህም የዕርድ ክፍል፣ የእንስሳት ማቆያ እና የሥርጭት ተሽከርካሪዎች ጥገናና ዕድሳት መከናወኑን ጠቅሰዋል፡፡

የቅድመ እና ድኅረ ዕርድ ምርመራ ከተደረገ በኋላ የዕርድ አገልግሎቱ ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን ጠብቆ እንደሚከናወንም ነው የገለጹት፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገኙ ከ3 ሺህ በላይ ሥጋ ቤቶች አገልግሎቱ እንደሚሰጥም ነው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የተናገሩት፡፡

ተገቢውን የምርመራ ሂደት ያላለፈ ሕገ ወጥ ዕርድ ለጤና ጠንቅ መሆኑን፣ ሕገ ወጥ ዕርድ የሚከናወነው ከታክስ ሽሽት ስለሆነ ሀገር ከዘርፉ ማግኘት ያለባትን ገቢ ስለሚያሳጣ እንዲሁም የአካባቢ ብክለትን እንደሚያስከትል በመገንዘብ ሕብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግም ጥሪ አቅርበዋል።

በዮሐንስ ደርበው

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.