ቢዝነስ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለጋራ መኖሪያ ቤት ደንበኞቹ የ3 ወራት የብድር መክፈያ እፎይታ ሰጠ

By Tibebu Kebede

April 16, 2020

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 8፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝ ምክንያት በማድረግ ለጋራ መኖሪያ ቤት ደንበኞቹ የሶሰት ወራት የብድር መክፈያ እፎይታ ጊዜ መስጠቱን አስታወቀ።

በዚህም ባንኩ ከደንበኞቹ መሰብሰብ የሚችለውን ከግማሽ ቢሊየን ብር በላይ ብድር ወደቀጣይ ጊዜ ማስተላለፉን ነው የገለጸው።