Fana: At a Speed of Life!

በቱርክ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በመሬት መንቀጥቀጥ ጉዳት ለደረሰባቸው ቱርካውያን ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 3 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቱርክ የሚኖሩ የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ክፍሎች በመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ቱርካውያን አስቸኳይ የቁሳቁስ፣ የገንዘብ፣ እና የጉልበት ድጋፍ ማድረጋቸው ተገለጸ፡፡

ድጋፉን በሀገሪቷ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር በመተባበር አድርገዋል ነው የተባለው፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ከቱርክ ጋር ጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዳለው ይታወቃል፡፡

እንደሚታወሰው አደጋው በደረሰበት ወቅትም ከመከላከያ ሠራዊት፣ ከፌዴራል ፖሊስ እና ጤና ሚኒስቴር የተውጣጣና 27 የፍለጋ እና ሕይወት አድን ባለሙያዎች ቡድን ከዕርዳታ ቁሳቁስ ጋር ወደ ሥፍራው መሄዱ አይዘነጋም፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.