Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ስሎቬኒያ ሴቶችን ማብቃት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ በጋራ ለመስራት ተስማሙ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 3 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ገጠራማ አካባቢዎች የሚኖሩ ሴቶችን ለማብቃት ከስሎቬኒያ ጋር ብትብብር ለመሥራት ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

የሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተሥፋዬ (ዶ/ር) ከስሎቬኒያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ታኒያ ፋየን ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በኢትዮጵያ ሴቶችን በማብቃት የቤተሰብ ብልፅግናን ማረጋገጥ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ መክረዋል፡፡

በኢትዮጵያ በተለይም ገጠራማ አካባቢዎች የሚኖሩ ሴቶችን ለማብቃት በጋራ ለመስራት መስማማታቸውንም ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኤርጎጌ ተሥፋዬ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ መንግስት ሴቶችን በኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች ለማብቃት ያለውን ቁርጠኝነት አስረድተዋል፡፡

ኢትዮጵያ ያላትን ዕምቅ ሐብትም የገለጹላቸው ሲሆን በተወያዩባቸው ጉዳዮች ላይ እና በልማቱ ዘርፍ ከስሎቬኒያ በጋራ ለመሥራት ያላትን ጠንካራ ፍላጎት ገልጸዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.