የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ ሀገር-በቀል ኢኮኖሚ ላይ በትኩረት እንደምትሠራ ገለጸች

By Alemayehu Geremew

April 12, 2023

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)ኢትዮጵያ ሀገር-በቀል ኢኮኖሚ ላይ በትኩረት እንደምትሠራ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ አስታወቁ።

ሚኒስትሩ “ከዕዳ መውጣት ፣ ዕድገት ማስመዝገብ” በሚል መሪ ቃል አሜሪካ በተዘጋጀው በዓለም አቀፉ የኢኮኖሚ መድረክ የፓናል ውይይት ላይ ተሳትፈዋል።

ዓለም ባንክ እና ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም እንዲሁም የግሉ ዘርፍ የፋይናንስ ተዋንያን እና ሌሎች የገንዘብ ተቋማት ኢትዮጵያ የምንዛሬ አቅርቦት ዕጥረቷን ለመፍታት የምታደርገውን ጥረት እንዲደግፉ ጠይቀዋል፡፡

በጉባዔው ከዓለም ባንክ በተጨማሪ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም እንደተካፈለም ተጠቁሟል፡፡