Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ክልል የጤና ተቋማትን መልሶ ለማደራጀት የሚያስችል ጉብኝት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል የጤና ሥራዎችን ለማየት እና ተቋማቱን መልሶ ለማቋቋም የሚያስችል ጉብኝት እየተካሄደ ነው፡፡

ከጤና ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት የተውጣጡት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ልዑካን ቡድን በጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ መሪነት በትግራይ ክልል ጉብኝት እያደረጉ ነው፡፡

ልዑካን ቡድኑ በግጭት ወቅት ጉዳት የደረሰባቸውን እንዲሁም አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙ ሆስፒታሎችንና ጤና ጣቢያዎችን በሁለት ቡድኖች በመሆን ተዘዋውሮ ጎብኝቷል።

በጉብኝታቸው የፀጋይ ገ/ር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል፣ ፋፂ ጤና ጣቢያ ፣አዲግራት ጀነራል ሆስፒታል ፣ ፍረወይኒ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል፣ ድንግለት ጤና ጣቢያ፣ ኣቢ አዲ ጠቅላላ ሆስፒታል፣ እዳጋ አርቢ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ፣ ማይቀንጠል እና ነብሌት ጤና ጣቢያዎች መዳሰሳቸውን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘው መረጃ ያመለክታል፡

ለቡድኑ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር አማኑኤል ኃይሌ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በአሉላ አባ ነጋ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.