Fana: At a Speed of Life!

የአውሮፓ ሀገራት ከፍተኛ ባለስልጣናት የሚያደርጉት ጉብኝት ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ ለሚደረገው ጥረት እውቅና የሰጠ ነው – የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 4 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ሀገራት ከፍተኛ ባለስልጣናት በኢትዮጵያ የሚያደርጉት ጉብኝት ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ ለሚደረገው ጥረት እውቅና የሰጠ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ አለም ሳምንታዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም የስሎቬኒያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ታኒያ ፋዬን እና የጣሊያኗ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ ጉብኝት ኢትዮጵያ ከአጋሮቿ ጋር ያላትን ግንኙነት በፍጥነት ወደ ነበረበት ለመመለስ የምታደርገውን ጥረት ያረጋገጠ ነው ብለዋል።
በተጨማሪም ጉብኝቱ ኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ ለምታደርገው ጥረት እውቅና የሰጠ ነው ማለታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።

ቃል አቀባዩ በመግለጫቸው በኢትዮጵያ ያሉ የቢዝነስ እድሎችን የሚያስተዋውቁ እና ባለሃብቶች ኢትዮጵያን እንዲመርጡ ለማስቻል ያለሙ ፎረሞች እና ኤክስፖ መካሄዱን አስረድተዋል።

አያይዘውም ዓለም አቀፉ የጥቁሮች ታሪክ፣ ቅርስ እና የትምህርት ማዕከል ልዑካን አዲስ አበባ መግባታቸውን ጠቅሰዋል።

ልዑኩ በቆይታው በአዲስ አበባ ዋና ጽህፈት ቤቱን መክፈት በሚችልበት አግባብ ላይ ከመንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር እንደሚወያይ ገልጸዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.